ግብጽ ለኤርትራ ባጓጓዘቸው የእርዳታ እቃዎች ላይ የተላለፉ ሀሰተኛ መረጃዎች
በሴፕቴምበር 1, 2025 ከ213 ሺህ በላይ አባላት ባሉት' የዶ/ር አብይ አህመድ የሁልጊዜ ደጋፊዎች/ supporters of Dr.Abiy Ahmed' የሚባል የፌስቡክ ግሩፕ ግብፅ በኤርትራ በኩል ኢትዮጵያን ለማጥቃት እየተዘጋጀች መሆኗንና ወደ አስመራ የጦር መሳሪያ መላኳን ከምስል ጋር አያይዞ አጋርቷል።

በGoogle reverse image እና በYanet የተደረጉ የተገላቢጦሽ የምስል ፍለጋዎች እንደሚያሳዩት ይኸው ምስል ቀደም ብሎ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 29 ቀን 2025 ኢአርጂ ዴቨሎፕመንት በተባለው ገጽ “በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ወንድማማችነት ግንኙነት በማስፋት ግብፅ የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ኤርትራ መላኳን በገለፀችበት ወቅት የተነሳ ነው።

ከዚህም በላይ የዚያን ቀን ይፋ የሆኑ ሪፖርቶች ይህንን ትክክለኛ ጭነት እንደ ሰብአዊ እርዳታ እንጂ እንደ ጦር መሳሪያ አይገልጹም። የግብፅ አጋርነት ኤጀንሲ በነሀሴ 29 በአስመራ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የህክምና ቁሳቁሶችን ጭኖ መድረሱን የሚያሳይ ነው።እርዳታው የዓይን ህክምና እና የኩላሊት እጥበት መሳሪያዎችን ያካተተ ለኤርትራ የፋርማሲዩቲካል አስተዳደር የሚሰጥበትም ነበር።

እነዚህ ዓይነት የሀሰት መረጃዎች በህዝብ መካከል ፍርሃትና የፖለቲካ ግጭት ሊያበረክቱ ስለሚችሉ በጥንቃቄ መቀበል አስፈላጊ ሲሆን ከማጋራት በፊት መመርመርና ማሰላሰልም ይጠበቅብናል።
ፀሃፊ: ሞላ ባህሩ