post-thumb

የቻርሊ ከርክን ግድያ ተከትሎ ትራምፕ የሰጡት መግለጫ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተፈጠረ ነው?

የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የወጣቱን የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊ ወዳጃቸው የሆነውን የወጣቱን ቻርሊ ከርክ ግድያ ተከትሎ የሰጡት መግለጫ የብዙሃኑን ትኩረት ስቧል።

በተለይም በቀድሞው ቲዊተር ወይም በአሁኑ X የትራምፕ ቪዲዮ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተሰራ( ai generated) ነው ብለው ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

በቻርሊ ከርክ ላይ የተፈጠረው ምን ነበር?

ክስተቱ የተከሰተው በ ፈረንጆቹ አቆጣጠር መስከረም 10,2025 ሲሆን ሰአቱ ከምሽቱ 3 ሰአት ከ 10 (Local Time) ነበር። በ Utah valley university  3000 በላይ ሰዎች በታደሙበት ቻርሊ ከርክ ንግግር እያደረገ ሳለ ከህንጻዎቹ በአንዱ ጣሪያ ላይ ካለ ቦታ በተተኮሰ ጥይት የ31 አመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቻርሊ ከርክ አንገቱ አካባቢ በመመታቱ ህይወቱ አልፏል።ጉዳዩ የበርካታ ሚዲያዎችን ትኩረት ስቦ የነበረ ሲሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕም ይህን ተከትሎ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የትራምፕ የመግለጫ  ቪዲዮ መቼ ተለቀቀ?

ይህ ቪዲዮ የተለቀቀው ከ ለሊቱ 10፡ 15  በፈረንጆቹ መስከረም 11, 2025  ላይ ሲሆን ከክስተቱ 7 ሰአት በኋላ እንደተለቀቀ ይህ ምስል ያሳያል።

ቪዲዮው በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተሰራ ነው?

ይህንን ቪዲዮ እውነት ወይም በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተሰራ ብለን ለመፈረጅ በመጀመሪያ ቪዲዮውን በጥልቀት መመልከት ሲገባ በመጀመሪያ የቪዲዮው ጥራት እንዲሁም የትራምፕ አወራር እና አኳሃን ቪዲዮው በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተሰራ የሆነ እንዲመስል አድርጓል

ይህንን የፕሬዚዳንቱን ቪዲዮ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ስለመሰራቱ ለማረጋገጥ 3 ደረጃዎችን የተሻገረ ምርመራ ተደርጓል።

  1. ቪዲዮው ውስጥ ያሉ ወይም የገቡ ሁሉንም ነገሮች መለየት እና የነዛን ነገሮች እውነተኝነት ማረጋገጥ

    በቪድዮው ውስጥ ጠረጴዛ፣ ከፕሬዚዳንቱ ጀርባ የተቀመጡ ፎቶዎች፣የተለያዩ ማለትም የአሜሪካ፣ የወታደራዊ ክፍሎች እና የፕሬዚደንሺያል ባንዲራ፣ፕሬዚዳንቱ የተቀመጡበት ወንበር እና ከትራምፕ በላይ የማይክሮፎን ማቀፊያ ሲታይ እነዚህ ነገሮች በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተሰሩ እንዳልሆኑ ማረጋገጥ ይቻላል።

  2. ከፕሬዚዳንቱ ጀርባ ባለው መስታወት ነጸብራቅ ፍንጭ ለማግኘት የተደረገ ሙከራ 

    ቪዲዮውን በዝቅተኛ ብርሃን(low light) በምንመለከትበት ጊዜ ከትራምፕ ፊትለፊት የካሜራ ባለሙያዎች እንዳሉ እና ሌሎችም ሰዎች እንዳሉ ለማወቅ ይቻላል። ይህም ቪዲዮው በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተሰራ እንዳልሆነ ተጨማሪ ፍንጭ ቢሆንም  በዛው ልክ ደግሞ የሚያጠራጥር ነገር አልታጣም።በቪዲዮው ከ18 እስከ 20ኛው ሰከንድ ድረስ የትራምፕ እጅ glitch እንደሚያደርግ ያሳያል። ለዚህም ሲባል ወደመጨረሻው ደረጃ መሸጋገር የግድ ብሏል።

  3. 'AI DETECTORS' ምርመራ 

    ለምርመራው Hive moderation Ai content ተብሎ የሚጠራ መተግበሪያ ጥቅም ላይ ሲውል ሲሆን የተገኘው ውጤትም ከስር ያለውን ይመስላል።

    ማጠቃለያ

    ቪዲዮው ምንም ያክል በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተሰራ ቢመስልም የታለፉ ሂደቶች ቪዲዮው በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተሰራ(AI GENERATED) ለመሆኑ ምንም ማስረጃ አይሆኑም። ምንም እንኳን ሂደቶቹ ቪዲዮው በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ስለመሰራቱ ማስረጃ ባይሆኑም ምናልባት ግን ቪዲዮው በሰው ሰራሽ አስተውሀሎት የተቀነባበረ( AI EDITED) ሊሆን ይችላል።

    ፀሃፊ: አቡበከር