post-thumb

በአፋሮች ዘንድ ልጆች ስጋ እና ምግብ በአንድ ቀን ውስጥ ከተመገቡ ለበሽታ ይዳረጋሉ የሚል ምልከታ አለ ምን ያህል እውነት ነው ?

በአፋር ማህበረሰብ ውስጥ ስጋ እና ቅባታማ የእንስሳት ተዋፅኦ የተመገበ ሰው ምግብ ቢበላ ቀጥታ ለተለያዩ በሽታዎች ይዳረጋል በማለት ያምናሉ። በዚህ ምክንያት በሳይንሱ ዓለም የተረጋገጠውን የሰው ልጅ የተመጣጠነ ምግብ የመመገብ ጉዳይ በማህበረሰቡ ችላ ስለተባለ ብዙ ሰው የተመጣጠነ ምግብ ባለማማግኘቱ ለተለያዩ በሽታዎች እየተዳረገ ይገኛል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነው የእንስሳት ጤና ዶክተር አቶ መሐመድ አወል (ዶ/ር) እንደሚግሩን ከሆነ የአፋር ማህበረሰብ ለረጅም ጊዜ ባለው የተሳሳተ ውሳኔ ለተለያዩ በሽታዎች ይጋለጣሉ ብለዋል።

እንደ አቶ መሐመድ ገለፃ፤ ከእነርሱ የአስተሳሰብ ገፅታ በተቃራኒ ሳይንሱ "የሰው ልጅ በቀን አራት ዓይነት የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት አለበት" ይላሉ።

አቶ ሐሰን በከል ደግሞ በአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ፤ ኪላይቶ መንደር ነዋሪና በማህበረሰቡ የአስተሳሰብ ደረጃ የሚያስቡ ናቸው። አቶ ሐሰን እንደሚገልፁት ከሆነ "እኛ አፋሮች ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በዚህ አስተሳሰብ የኖርን በመሆኑ፤ ጉዳዩም በየጊዜው እንደ እሳቤያችን የሚከሰት ነው፤ ልጆች ስጋ እና ምግብ በአንድ ቀን ውስጥ ከተመገቡ ለበሽታ ይዳረጋሉ" የሚል መልስ አላቸው።

ታዲያ ይህን የሳይንሱን እና የማህበረሰቡን አስተሳሰብ ለማስታረቅ እንደ መረጃ የተጠቀምነው የዶክተር መሐመድ አወል ገለፃ ሲሆን ከተለያዩ የአካዳሚክ መረጃዎች በመነሳት የሰው ልጅ ስጋ እና ወተት እንዲሁም የወተት አስተዋፅኦን ከተለያዩ ምግቦች ጋር በ24 ሰዓት ውስጥ መጠቀሙ ጉዳት የለውም፤ በተቃራኒ እነዚህን በጋራ መመገብ የበለጠ ጤናማ ያደርጋል።


 በካሚል መሐመድ (ሠመራ)