በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም የተከፈቱ ሀሰተኛ ገጾች በየትኞቹ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ይገኛሉ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በሚል ስም በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በርካታ ሀሰተኛ ቻናሎች ተከፍተው ይገኛሉ፡፡ ትክክለኛው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ገጾች ንቁ ሆነው የሚገኙት በቴሌግራም እና በ ኤክስ ገጾች ላይ ብቻ ሲሆን፤ በዩቲዩብ፣ በቲክቶክ እና በፌስቡክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ምንም አይነት ገጾች የሉትም፡፡

ከላይ የምትመለከቷቸው ምስሎች በቴሌግራም መተግበሪያ ላይ የሚገኙ ሀሰተኛ ገጾች ሲሆኑ፤ በተለይም የቴሌግራም ግሩፖችን በስፋት ይጠቀማሉ፡፡ ስያሜውን በተመለከተም ቲክቫህ ከሚለው ስም ቀጥሎ ልክ በትክክለኞቹ ቻናሎች ይዘት ነክ ስያሜዎች እንደሚሰጣቸው ሁሉ ተመሰሳይ መንገድ በመጠቀም ሌሎች ስያሜዎችን አስከትለው የተፈጠሩ ናቸው፡፡
በቴሌግራም ላይ የሚገኙት የሀሰተኛ ገፆች በተለይም እስከ 80 ሺ የሚጠጋ ተከታይ እንዳላቸው በሚጠቅሰው ግሩፕ ብዙ አሳሳች እና የማስተዋወቂያ ይዘቶችን ያሰራጫሉ። በዚህ ላይ ትልቁ ለማጭበርበሪያ የሚጠቀሙት የተመልካቾችን ቁጥር ማጭበርበር ነው ይህም ብዙ እይታ እንዳለው በማስመሰል በዚህ ያማልላሉ ፡፡
ይህ ቁጥር ትክክለኛ የተመልካች ቁጥር ሳይሆን በቴሌግራም ቡቶችን በመጠቀም የሌሉ ሰዎች ዜናውን እንደተመለከቱት በማስመሰል የሚቀርብ ነው፡፡ ይህም ለምሳሌነት ከላይ የተጠቀሱ ምስሎችን ብንመለከት የተከታይ ቁጥርራቸው 80 ሺ የሆኑ ግሩፖች የተመልካቻቸው ቁጥር እስከ 600 ሺ ይደርሳል ፡፡
የቴሌግራም ቦት በመጠቀም እይታን የሚጨምሩ ልጥፎችን እንዴት መለየት እንችላለን ?
- ፖስቶቹ እይታቸው ትልቅ ቁጥር ቢያሳይም ምንም አይነት ሪአክሽን ላቸውም፣
- በተመሳሳይ ማስታወቂያ በጣም የተራራቀ የእይታ መጠን ያሳያሉ፣
- ወጥ የሆነ የእይታ መጠን የላቸውም፣
- አብዛኞቹ ተከታዮች ንቁ ተከታታይ አይደሉም፣
የቻናሉን እውነተኝነት ለመጠበቅ ቲክቫህ ኢትዪጵያ የሚሰራቸውን ዜናዎች ቀጥታ ሲጠቀሙ ሌላው በስፋት ያልተረጋገጡ የክሪፕቶ መረጃዎችን ያጋራሉ፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሚጠቀመው የፌስቡክ ገጽ አለው?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ገጾቹ ላይ እነዳሰፈረው የሚጠቀምበት የፌስቡክ ገጽ የለውም፡፡ ሆኖም ግን በፌስቡክ ላይ በርካታ ሀሰተኛ ገጾች በስሙ ተከፍተው የተለያዩ መረጃዎ ይሰራጫሉ፡፡

በፌስቡክ ላይ 121 ሺ አባላት ያሉት ግሩፕን ጨምሮ ከ40 ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት ገጽ ከትክክለኛዎቹ የቲክቫህ ገጾች መረጃዎችን በመቅዳት የሚያደርስ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ሎሎች ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያልሰራቸውን ዜናዎች ሲያጋራ በስፋት ይስተዋላል፡፡

ልክ እንደ ፌስቡክ ሁሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የዩቲብ ቻናል እንደሌለው ገልጧል፡፡ እነዚህ ሀሰተኛ ገጾች በስፋት መረጃችን በዩቲዩብ ሲያጋሩ የነበረው በግጭት ወቅቶች ጊዜ እና ወቅት ጠብቀው በርካታ ሰዎች ሊመለከቷቸው የሚችሉ ርዕሰ ጉዳዮች ሲነሱ እንደሆነ ካየናቸው ሀሰተኛ ገጾች መረዳት ችለናል፡፡
ቲክቶክ ላይ በተመሳሳይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንም አካውንት የሌለው ሲሆን በስሙ የተከፈቱ ሐሰተኛ አካውንች ግን በዚህም አሉ፡፡ በቲክቶክ በርካታ የቲክቫህ ዜናዎች በስፋት የሚሰራጩበት ነው፡፡ አንዳንድ ቲክቶከሮች ዜናውን በማንበብ ለተከታዮቻቸው ያደርሳሉ አንዳንዶቹም ምንጭ ሳይጠቅሱ የቲክቫን ዜና የራሳቸው በማስመሰል ያቀርባሉ ፡፡
ትክክለኞ የቲክቫህ ገጾች የትኞቹ ናቸው ?

ከላይ በምስል በተቀመጠው መሰረት ቲክቫህ ተከታዮቹ ገጾች አሉት በተጨማሪም የቲክቫን ትክክለኛ ገጾች ለመረዳት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ባለው የቴሌግራም ቻናል ላይ ባለው መግለጫ ዋናውን ቻናል እና በስሩ የሚያስተዳድራቸውን 5 የቴሌግራም አካውንቶች ያስቀምጣል፡፡ በእሱ ማረጋገጥና የቲክቫህን ዜናዎች በቀጥታ በእነዚህ ቻናሎች መከታተል ይመከራል፡፡