ያሬድ ገ/ስላሴ ወደ ውጪ ሸሽቷል የሚለው ወሬ እውነታ
ወጣት ያሬድ ገ/ስላሴ የተባለ ልጅ ዘውዱ ሃፍቱ ላይ በፈጸመው የግድያ ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ሐምሌ 04 ቀን 2017 ዓ.ም የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል ።
በወጣት ያሬድ ገ/ስላሴ ላይ የተሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ የሚገልጹ በፌስቡክ በጽሁፍ እና በፎቶ ተደግፎ በማህበራዊ ሚድያ ሲዘዋወሩ ተመልክተናል ። በፌስቡክ የተሰራጨው መረጃ በሺዎች የሚቆጠሩ የማህበራዊ ሚድያ ተመልካቾች እይታ በማግኘቱ የተነሳ የማረሚያ ቤቱን ስራ አስኪያጅ ምክትል ኮሚሽነር አማኑኤል ፍስሃን ማብራሪያ ጠይቀናል።
በዚህም በአሁን ስዓት ያሬድ ገ/ስላሴ መቐለ በሚገኘው ማረሚያ ቤት ታስሮ እንደሚገኝ ባደረግነው ማጣራት ለማወቅ ችለናል። ይህ መረጃ ሊሰራጭ የቻለበት ዋነኛው ምክንያት የወጣት ያሬድ ገ/ስላሴ አባት ከጦርነት በፊትም ሆነ ከጦርነቱ በኃላ የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር በመሆን ያገለገለ ሲሆን በአሁኑ ስዓት ደግሞ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ታጣቂዎች አርሚ 22 የበላይ አዛዥ በመሆን የሚመራ በመሆኑ እና ከጸጥታ አካላት ባለው ቅርበት በመነጋገር እና ብር በመክፈል ከሀገር እንዲሸሽ አድርጎታል በሚል ምክንያት እንደሆነ ከሚሰራጨው መረጃ ለመረዳት ችለናል።
መረጃ ሊሰጡን የጠየቅናቸው የማረሚያ ቤት ስራ አስኪያጅ ምክትል ኮሚሽነር አማኑኤል ፍስሃ መረጃው የተሰራጨው ነሃሴ 14 ቀን 2017 ዓ/ም እንደሆነ በመግለጽ፡-
‹‹እየተወራ ያለው መረጃ እውነት የለውም ከእውነት የራቀ ውሽት ነው። ከሀገር ሽሽተዋል የሚባለው ልጅ በቀኑ ራሴ በአካል አግኝቼዋለሁ ስለዚህ እንዲህ አይነት ክፍተትም ሆነ የጠፋ ሰውም የለንም። በማህበራዊ ሚድያ የሚያሰራጩ ሰዎችም ሆኑ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች በዓላማ እንዲህ አይነት መረጃ ሊያሰራጩ ይችላሉ በአባቱ ምክንያት የተነሳ እንዲህ ሊሉ ይችላሉ ። በትግራይ ክልል ባለው የፖለቲካ ችግር እና ትርምስ እንደሆነም ይታወቃል" ሲሉ ገልጸዋል።
ሰለዚህ በማህበራዊ ሚድያ የተሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ በማየት እና በመሰማት ህብረትሰቡ የተዛባ አመለካከት እንዳይዝ የተጠናከረ ስራ ያስፈልገናል ሲሉ ገልጸዋል ። ወጣት ያሬድ ክስ ተመስርቶበት ፍርዱን እስኪጨርስ ድረስም በማረሚያ ቤቱ እንደሚቆይ በመገልጽ እሰከአሁን ድረስ በማረሚያ ቤቱ እንዳለ ገልጸውልናል ። ‹‹ይህንን መረጃ እውነተኛነቱን ለማጣራት የሚፈልግ ማነኛው ሰው ወደ ማርሚያ ቤቱ ድረስ በመምጣት እውነቱ ማረጋገጥ ይችላል›› ሲሉ መልእክታቸው አስተላልፈዋል ።
ፀሃፊ: ፊሊሞን ደስታ