ከባድ መሳሪያዎችን እንዲሁም የድሮን ጥቃትን አስመልክቶ የተሰራጩ የተሳሳቱ ዘገባዎች
የከባድ የጦር መሳሪያዎቹን እንቅስቃሴ በተመለከተ የተሰራጨ ሃሰተኛ ዘገባ
በቅርብ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተለይም በቲክ ቶክ ላይ የወጣው አንድ ቪዲዮ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ህዝብን ሲረብሽ እንደነበር የሚታወስ ነው። ቪዲዮው ከባድ የጦር መሳሪያዎች ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ከተማ እየተጓጓዙ ነው የሚል መረጃ ይዞ ነበር ። ይህ መረጃ ከበስተጀርባው ከባድ ስሜታዊ እና ፖለቲካዊ ውጥረቶች ባሉበት ሁኔታ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ።

ሞስል 1 : የተቀነባበር የውሸት የጦር መሳሪያ ፖስት በቲክቶክ መለቀቁን ያመለክታል
የውሸት ዘገባው ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ከተማ የጦር መሳሪያ ሲጓጓዝ ብሎ በሰበር መረጃነት ሲያጋራው" በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና እንቃወማለን፡ ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር ሲጓጓዝ የወጣው ከባድ መሳሪያ ነው” ብሎ አጋርቶታል።
በተለቀቀበት ጊዜም የመረጃውን አሳሳቢነት "ባህር ዳር የአማራ ክልል ዋና ከተማ ነች፥ በክልሉ እየተካሄደ ያለው የትጥቅ ግጭት ለሞት እና ለሰብአዊ ቀውስ ምክንያት ሆኗል ፥በተለያዩ የአማራ ዞኖች በጎጃም፣ በሰሜን ሸዋ፣ በጎንደር እና በወሎ ላይ ጦርነት መቀጠሉን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል" በማለት አሰራጭቷል።
የዘገባውን ሃሰተኛነት ለማረጋገጥ የተደረጉ ምርመራዎችና ውጤቶች
በተጋራው የተሳሳተ መረጃ ላይ ከባድ የጦር መሳሪያዎቹ ወደ ባህር ዳር እየተጓጓዙ ነው በሚል የተጋራው ምስል የተወሰደው በጥቅምት 2023 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ከተደረገ ወታደራዊ ትርዒት ነው። ይህንንም ፔሳቼክ (pesacheak) እና google reverse image በመጠቀም ምስሉን በመመርመር እና ከሌሎች ኦሪጅናል ቪዲዮዎች ጋር በማነጻጸር ተመሳክሯል። የተረጋገጠው ምስልም ከዚህ በታች ቀርቧል።

ምስል 2: ትክክለኛው ምስል[ ፋና ቲቪ]
በምስል ግልበጣ /google reverse image የተገኘ ውጤት እንደሚያሳየው ምስሉ በጥቅምት 2023 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተደረገው ወታደራዊ ትርዒት ላይ የተነሳ መሆኑ ተረጋግጧል። በተጨማሪም ይህ ዘገባ ውሸት ለመሆኑ ተጨማሪ ማረጋገጫም የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል የወታደራዊ ትርኢቱን ቪዲዮ በጥቅምት 23 ቀን 2023 ፥ ከቀኑ 20፡50 ጀምሮ እንደተሰራጨ ተረጋግጧል።
በባህር ዳር ከተማ በድሮን ጥቃት የእሳት አደጋ ስለመድረሱ የተዘገበ የተሳሳተ መረጃ
ሌላኛው የተሳሳተ መረጃ በባህርዳር ከተማ በድሮን ጥቃት ህንፃ መቃጠሉ ሲሆን በዘጋቢው ፖስት ስርም "ይህ አሁን የደረሰን አሳዛኝ ሰበር ዜና ነው ባህር ዳር ዛሬ በድሮን እና በከባድ መሳሪያ ጥቃት ተፈጽሞባታል በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ለአለም እንዲደርስ ሼር እና ኮፒ ያድርጉ" በሚል የተሳሳተ መረጃ አጋርቷል።
የዘገባውን ሃሰተኛነት ለማረጋገጥ የተሰሩ ምርመራዎችና ውጤቶች
የእሳት አደጋ የሚለውን ቁልፍ ቃል በመጠቀም በዩቲዩብ ላይ በተደረገ ፍለጋ ቪዲዮው የባህር ዳር እንዳልሆነ ተረጋግጧል። ቪዲዮው ከዚህ ቀደም በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ-AMN ዩቲዩብ ቻናል ላይ የተለጠፈ እና በፌስቡክ ገጽ በጥቅምት 30 ቀን 2021 የተጋራ ነው። በምስሉ ላይ ያለው የህንፃ ቃጠሎም በአዲስ አበባ ውስጥ በእሳት ላይ ያለ ሕንፃ ነበር። በተጨማሪም "በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ እህል በረንዳ በሚገኘው አማኑኤል ጸጋ ህንጻ ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ በሰው ላይ ቀላል የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት አድርሷል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና የአካባቢው ማህበረሰብ እሳቱን በቁጥጥር ስር አውለዋል" ሲል አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል ።
መረጃዎችን ለማረጋገጥ ተግባሮ ላይ የዋሉ አጋዥ መሳሪያዎች
- Google revers image/የምስል ግልበጣ
- Pascheak/ፓስቼክ
- Addis media network/አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
- Tnews youtube channel ናቸው::
የመረጃው ተጽዕኖ ፥ ለህዝቡ የተሰጠ ግንዛቤ እና መረጃዎችን በማጣራት ሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች የመረጃው ተጽዕኖ ይህ የተሳሳተ መረጃ በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደረ መረዳት ይቻላል። በተለይም በባህር ዳር ከተማ ወታደራዊ መሳሪያዎች እየተጓጓዙ ነው የሚለው መረጃ በከተማው ነዋሪዎች ዘንድ ፍርሃትና ስጋትን ፈጥሮ ነበር።
የሰዎች የስነ-ልቦና ሁኔታ እንዲረበሽ እና የሰላም እጦት ስሜት እንዲሰማቸው አድርጓል። በተመሳሳይ መልኩ የቃጠሎው ቪዲዮ በባህርዳር የተፈጠረ አዲስ አደጋ እንደሆነ ተደርጎ በመሰራጨቱ ህዝቡ በድንጋጤና በብስጭት ውስጥ እንዲወድቅ ምክንያት ሆኖ እንደነበር ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው ሰዎች ተናግረዋል። ለህዝቡ የተሰጠ ግንዛቤ በእነዚህ የተሳሳቱ መረጃዎች ምክንያት የህዝቡ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለቀቁ መረጃዎችን ያለማጣራት የመቀበል አዝማሚያ አሳይቷል። ይህ ደግሞ በህብረተሰቡ ውስጥ የመረጃ ንቃተ ህሊና (information literacy) ዝቅተኛ መሆኑን የሚያሳይ ነው። የመረጃ ምንጩን አለማመን ቪዲዮዎችን ከቀደሙ አደጋዎች ጋር ማያያዝ እና ከመረጃ ጀርባ ያለውን እውነት መመርመርን የመሳሰሉ ጠቃሚ ክህሎቶች እንደጎደሉ መታዘብ ይቻላል።
መረጃዎችን በማጣራት ሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች
አብዛኛው የተሳሳተ መረጃ የተሰራጨው ታማኝ ባልሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ነው። ይህም ትክክለኛውን መረጃ ከየት ማግኘት እንደሚኖር በማድረግ ፈታኝ ነበር። የውሸት መረጃዎች በፍጥነት በመሰራጨታቸው የምስል እና ቪዲዮ ማጣሪያ መሳሪያዎች ችግር ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች ከድሮ ክስተቶች የተወሰዱ ስለነበሩ እነሱን ለማጣራት እና ትክክለኛ ምንጫቸውን ለማግኘት የቴክኖሎጂ እገዛ የሚያስፈልግበት ሁኔታ ነበር።
ፀሃፊ:ሞላ ባህሩ