post-thumb

ዓለምን አነጋግሮ ያለፈው AI የፈጠረው ታሪክ ... ስለ ፈጠራ ታሪኮች ምን ያስተምረናል?

በቅርቡ በተለያዩ የማኅበራዊ ትስር ገጾች ጄሲካ ራድክሊፍ የተባለች አንዲት ሴት የምታሰለጥነው አሳ ነባሪ መበላቷን የሚገልጹ ዜናዎች በስፋት ተሰራጭተው ነበር።

 

 

ብዙዎች ተንቀሳቃሽ ምስሉን ተመልክተው የተሰማቸውን ሀዘን በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ ገፆች  ሲገልፁም ተመልክተናል። በሀገራችንም ይኸው ዜና ብዙዎች ወደ አማርኛ በመቀየር የተቀባበሉት ነበር።

ከዚህ ተንቀሳቃሽ ምስል ጋር ተያይዞ ያለው እውነታ ምንድን ነው?

የተለያዩ የ ፎረንሲክ ትንተናዎችም በተንቀሳቃሽ ምስሉ የሚታዩ ተፈጥሮአዊ ያልሆኑ የውሀ እንቅስቃሴዎች ወጥ ያልሆኑ የተንቀሳቃሽ ምስሉ ሂደት በ ሰውሰራሽ አስተውህሎት እንደተሰራ ማሳያ መሆናቸውን ያሳያሉ። 

የተለያዩ የዜና ምንጮች እንዳረጋገጡት ይሀ መሰል ክስተት በገኻዱ ዓለም አለመፈጠሩን ነው። በሀሰተኛ ዘገባው ላይ የተጠቀሰውና ድርጊቱ ተፈጽሞበታል የተባለው "ፓስፊክ ብሉ ማሪን ፓርክ" በእውኑ የሌለ ቦታ ነው።

እነዚህንና መሰል ተንቀሳቃሽ ምስሎች የ ሰውን ስሜት እና ትኩረት በ ቀላሉ የመሳብ አቅም አላቸው ይህም ለብዙ ሰዎች እንዲዛመቱ በተጨማሪም በቀላሉ ብዙ እይታ እንዲኖራቸው ያደርጋል።

ተመሳሳይ አይነት ታሪኮች ሲገጥሙን ምን እናድርግ ?

  • መሰል እውነተኛ ታሪኮች ተዓማኒ የሆኑ መደበኛ ሚዲያዎች የዜና ሽፋን የመስጠት እድላቸው ሰፊ ነው በመሆኑም ከዚያ ላይ ማረጋገጥ ተገቢ ይሆናል።
  • የፎቶ እና የቪዲዮ ይዘቶችን በጥልቀት በመመልከት አጠራጣሪነታቸውን በመጠኑም ቢሆን መለየት ይቻላል። ስለዚህ ይህንን የምንለይበትን ክህሎት ለወደፊቱ ማዳበር ጠቃሚ ይሆናል።
  • ሐሰተኛ መረጃዎች በተሰራጩበት ፍጥነት እውነተኛው መረጃ የመሰራጨት እድሉ አነስተኛ በመሆኑ አጠራጣሪ ሆነው ካገኙት፤ መረጃውን ለሌላ ሰው መልሶ አለማጋራት ይመከራል።